የቀዝቃዛ ሻወር ታምራዊ ጥቅሞች(Health Benefits of Cold Shower)

ስለ ቀዝቃዛ ሻወር ጥቅም ከመዳሰሳችን በፊት አንድ ቀላል እውነታ
እናስቀምጥ ሙቅ ሻወር መሠረታዊ ፍላጐት ሳይሆን ለመዝናኛነት እና
ቅንጦት የምንጠቀምበት ነው፡፡ በአብዛኛው የሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ
በቅርብ በሚያገኙት ውሃ ውስጥ ሻወር ይወስዳሉ፡፡ በሃይቅ ውስጥ
ዋኝተው የሚያውቁ
ከሆነ በቀላሉ ሊያስታውሱ የሚችሉት ነገር የውሃውን ቅዝቃዜ ነው፡፡
ግሪኮች በአንደኛው ክፍለ ዘመን ለህዝብ አገልግሎት የሚውል የሙቅ
ሻወር አገልግሎትን ፈጠሩ ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ አብዛኛዎቹ
ግሪካዊያን ካለው የጤና ጥቅም አንፃር ቀዝቃዛ ሻወርን ነበር የመረጡት፡፡
ታምራዊ ጥቅሞቹ እነሆ፦
1. ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በኋላ ቶሎ እንድናገግም ያረዳል!
አትሌቶች ከባድ ልምምድ ካደረጉ በኋላ የሚያጋትማቸውን ድካምና ህመም
ለመቀነስ በበረዶ ውሃ ሻወር ይወስዳሉ ወይም ይዘፈዘፋሉ እኛ ግን ያን
ያህል እርቀት መጓዝ አይጠበቅብንም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ጥቅም
ለማግኝት ከልምምድ በኋላ ቀዝቃዛ ሻወር መውሰድ ተገቢ ነው፡፡
2. ስብን (ፋት) ለማቅለጥ!
ሁለት የስብ አይነቶች በሰውነታችን ውስጥ ይገኛሉ ነጭ ስብ እና ቡናማ
ስብ። ነጩን ስብ እንደ መጥፎ ሰው እንቁጠረው ቡናማውን ደግሞ እንደ
ጥሩ ሰው፡፡ ነጩ ስብ ሁላችንም የምናውቀው የሰውነታችን ስብ ሲሆን
ሁላችንም ለማጥፋት የምታገለው ነው፡፡
ሰውነታችን ከሚፈልገው በላይ የሆነ ከፍተኛ ካሎሪ
በምንወስድበት ጊዜ በሃይል (Energy) መልክ እንዲጠፋ ማድረግ
ይሳነናል/ ያቅተናል በሃይል/ጉልበት መልክ ካልተወገደ ወይም ካልጠፋ
ግን ይህ ነጭ ስብ በታችኛው ጀርባችን፣ አንገት፣ ከዳሌ ከፍ ብሎ ባለው
የመካከለኛው ሰውነት ክፍል እና ከጉልበታችን ከፍ ብሎ ባለው የእግር
ክፍል ላይ ይከማቻል፡፡
ቡናማ ስብ ጥሩ ሰው ሲሆን የሚሰጠን ጥቅም ለሰውነታችን ሙቀት
መፍጠር ነው፡፡ በከባድ ቅዝቃዜ ወቅት እነዚህ ቡናማ ስቦች ይነሳሱና
ካሎሪን በማቅለጥ የሰውነታችን ሙቀት እንዲጨምር ያደርጋሉ ይህም
የሰውነት ክብደትን በመቀነስ ይረጋናል፡፡
3. የደም ዝውውርና በሽታን የመከላከል አቅምን ይጨምራል!
ስብን ለመቀነስ ቀዝቃዛ ሻወር እንዴት እንደሚረዳን ከላይ ተመልክተናል
ሰውነታችን ስብን ለማቃጠል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የበሽታ መከላከያ
ስርዓታችንን ያነሳሳል ይህም ቫይረስን የሚዋጉነጭ የደም ሴሎች
እንዲመረቱ ያደርጋቸዋል የእነዚህ ሴሎች መመረት በህመም የመጠቃት
እድላችን እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡ ቀዝቃዛ ሻወር አጠቃላይ የደም
ዝውውርን ይጨምራል ይህም የደም ቧንቧዎች እንዳይጠነክሩ እና የደም
ግፊት ያስወግዳል፡፡
4. የሚስብ ፀጉር እና ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል!
በሰውነታችን ላይ ያለውን ብጉር ለመቀነስ ቀዝቃዛ ሻወር ከፍተኛ ድርሻ
አለው። ሙቅ ውሃ ቆዳን ያደርቃል ቀዝቃዛ ውሃ ኩቲክልና ቀዳዳዎችን
በመዝጋት በቆሻሻ ከመደፈን ይከላከላል፡፡ ቀዝቃዛ ውሃ የሚያንፀባርቅና
በጣም የሚስብ ፀጉር እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ቀዝቃዛ ውሃ ኩቲክሎችን
በመዝጋት ቆሻሻ በራስ ቅላችን ላይ እንዳይከማች ይረዳል፡፡
5. ደስተኛ እና ፈጣን እንድንሆን ያደርጋል!
ጠዋት ከአልጋ ላይ ሲወርዱ ደብርዎትና ተጫጭኖዎት የሚይነሳ ማነው?
ይህ ሁሉም ሰው የሚያጋጥመው ነገር ይመስለኛል ነገር ግን ጠዋት ወደ
ስራ ከመሄድዎ በፊት ገና ከአልጋዎ እንደወረዱ ቀዝቃዛ ሻወር ይውሰዱ፡፡
ቀዘቃዛ ውሃ በሰውነትዎ ላይ በሚፈስበት ጊዜ ለቅዝቃዜው ምላሽ
በጥልቀት ይተነፍሳሉ ይህ ሰውነትዎ ኦክስጂን አወሳሰዳችን በመጨመር
ሰውነታችን ራሱን ለማሞቅ የሚያደርገው ሙከራ ነው፡፡የልብ ምትዎ
ይጨምራል የዚህ ውጤት ደም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን እንዲዳረስ
በማድረግ ጉልበት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡
መልካም ጤንነት!!

አቶ በረከት ስሞኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ

ግለሰቦቹ በጥረት ኮርፖሬት ፈጽመዋል ተብሎ በተጠረጠሩበት የሀብት
ብክነት ወንጀል አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በቁጥጥር
ስር ውለዋል።
አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ)ን በጥረት ኮርፖሬት
ከደረሰ የሀብት ብክነት ወንጀል ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በቁጥጥር
ስር መዋላቸውን የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ገልጿል።
የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ዝግአለ ገበየሁ ዛሬ
ረፋድ ላይ ጉዳዩን በተመለከተ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ሁለቱ
ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ወደ ባህር ዳር መወሰዳቸውን
አስታውቀዋል።
የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈፀመውም በክልሉ በመሆኑ ጉዳያቸው
በክልሉ ፍርድ ቤት እንደሚታይም ነው ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።
ኮሚሽኑ በእስካሁኑ ሂደት በግለሰቦቹ ላይ ክስ ለመመስረት
የሚያስችለኝን ከበቂ በላይ ማስረጃ ሰብስቢያለሁም ብሏል።