የጀርባ ህመም መነሻ ምክንያቶች እና መፍትሔዎች

መቼና የት እንደመጣ መነሻው ምን እንደሆነ በዉል ሳያዉቁት በጀርባ
ህመም ተሰቃይተዋል? የጀርባ ህመም በአደጋ ብቻ
ላይከሰት ይችላል የአቀማመጥ ሁኔታ የሚጠቀሙት ጫማ ከመጠን ያለፈ
ዉፍርትና ከባድ ነገሮችን ማንሳት የላይኛዉና ታችኛው ጀርባ ህመም
ያስከትላል።
በሴቶችና ወንዶች ላይ የጀርባ ህመም የሚያስከትሉ መነሻ ምክንያቶችን
በዝርዝር እንመልከታቸው፦
1. የቢሮ ወንበር!
የቢሮ ወንበርዎ ለጀርባ ህመም ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋሉ ሲቀመጡ
ጎበጥ የሚሉ ከሆነ ጀርባዎ ላይ ጫና ያደርጉበታል
አከርካሪ ሊጋመንታችን ከአቅም በላይ ይለጠጥና ዲስካችን የጀርባ
አጥንታችን እንዲወጠር ያደርጋል ከጊዜ ብዛት የጀርባ አጥንታችንን
በመጉዳት ለጀርባ ህመም ይዳርገናል።
2. የሚያደርጉት ጫማ!
ጫማ ለጀርባዎ ጤንነት ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል የማይገባ/ትክክል
ያልሆነ ጫማ አቋምዎን በማዛባት ማዕከላዊ የግራቪቲ ቦታን ያዛባል
ይህም በታችኛው የጀርባ ክፍልዎ ላይ ህመም ይፈጥራል።
3. የሚተኙበት ፍራሽ!
የሳሳ ፍራሽ መጠቀም የታችኛዉን የጀርባ ክፍል እንዲሰምጥ ያደርጋል
በተጨማሪም የአከርካሪ አጥንቶችን እንዲዛቡ በማድረግ
በጡንቻዎች እና የአከርካሪ መገጣጠሚያዎች ላይ ዉጥረት ይፈጥራል።
4. የጀርባ ቦርሳ!
የሚይዙት የጀርባ ቦርሳ ትልቅ ከሆነ ብዙ እቃዎችን የመያዝ እድል
ይኖርዎታል ተጨማሪ ሸክም በጀርባዎ ላይ መጫን ትልቁ የጀርና ህመም
ምክንያት ነው።
በአንድ በኩል ያለዉ የሰዉነት ክፍልዎ ላይ ሸክም መጨመር የአከርካሪ
አጥንቶች እንዲጎብጡ በማድረግ የጀርና ህመም እንዲከሰት ያደርጋል።
5. በሆድ በኩል መተኛት!
በሆድ በኩል ተደፍተዉ ሲተኙ በጀርባዎና በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ
ተጨማሪ ሸክም ይጨምራል በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ
ሸክም ጨመሩ ማለት ደግሞ የሙሉ ሰዉነትዎን ቅርጽ ያዛባዋል
ጭንቅላትዎን ወደ ጎን ሲያዞሩት ደግሞ ጭንቅላትዎንና አከርካሪዎት
ከመደበኛ አቅጣጫዎ ውጪ አደረጉት ማለት ነው።
6. ትከሻ ወይም አንገት ለረጂም ሰዓት አንገትን አዘንብሎ(ደፍቶ) መቆየት
ወይም መጓዝ!
በትከሻዎቻችን መሀል ያሉትን ጡንቻዎች እንዲዝሉ በማድረግ የላይኛው
ጀርባ ክፍል እና የአንገት ህመም ያስከትላል።
7. ላኘቶኘና ስማርት ስልኮች!
በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎቻቸው ፍቅር
ስለወደቁ በነዚህ ሰዎች ላይ የጀርባ ህመም የተለመደ ነው።
በስራ በተጠመድበት ወቅት ስልክዎትን በትከሻዎና በጆሮዎ መሀል
በመያዝ ለረጂም ጊዜ ማውራት የአንገት ህመም ያስከትላል።
8. ከመጠን ያለፈ ውፍረት!
ከሌሎች በሽታዎች በተጨማሪ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለጀርባ፣
መገጣጠሚያ እና ጡንቻዎች ህመም ያጋልጠናል። አብዛኛዎቹ
በሚኖራቸው ውፍረት በዳሌና በታችኛው የጀርባ ክፍል ህመም
ያጋጥማቸዋል።
9. እግርን አጣምሮ መቀመጥ!
እግርዎን አጣምረው በሚቀመጡበት ጊዜ የአከርካሪ አጥንትዎ ቀጥ ማለት
ይሳነዋል ይህም በዳሌ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ከመጠን
በላይ እንዲለጠጡ ያደርጋቸዋል። በተጨማሪም የደም ዝውውር
በመስተጓጐሉ ምክንያት ቫሪኮስ ቬይን(Varicose vein) ለተባለ በሽታ
ያጋልጣል።
10. ሲጋራ ማጨስ!
በሲጋራ ውስጥ ያለው ኒኮቲን ወደ ዲስክ(Disc) የሚሄደውን የደም
ዝውውር በመቀነስ የአከርካሪና ጐን አጥንት ችግር
ያስከትላል። በተጨማሪም ካልሲየም በአግባቡ ከሰውነታችን ጋር
እንዳይዋሀድ በማድረግ የአጥንት እድገትን ይገታል በመሆኑም ሲጋራ
የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች በአንድ እጥፍ የጀርባ ህመም ችግር
ያጋጥማቸዋል።

የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር

የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት የህመም
ዓይነት ነው ፡፡ በተለይ እድሜያቸው ከ 50 እስከ 60 ዓመት የሆናቸው
የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የመከሰት እድሉ ሰፊ ነው ፡፡
ህመሙ እንደ ግለሰቡ የዕድሜ ሁኔታ የሚሰራጭበት የሠውነት ክፍልም
በዚያው ልክ ይወሰናል ፡፡ ሴቶች ላይ ከዳሌያቸው በስተቀር ሁሉም
የመገጣጠሚያ አካባቢዎች ላይ የመከሰት እድል ሲኖረው
ቁርጭምጭሚት ፣ የእጅ መገጣጠሚያዎች ፣ ዳሌ እና ትንንሽ የአጥንት
ክፍሎች ደግሞ ሴቶችም ወንዶችም ላይ ይታያል ፡፡
የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር መነሻ ምክንያቶች
የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር መነሻ ምክንያቶች በሁለት ዓበይት
ክፍሎች ተከፍለው ሊታዩ ይችላሉ ፡፡
1. ቀዳማዊ የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር
ስር የሰደደ የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር የሚገናኘው ከእድሜ
መግፋት ጋር ቢሆንም መነሻ ምክንያቱ ግን የእድሜ መግፋት ጉዳይ
አይደለም ፡፡
በህክምናው ዘርፍ የተደረጉ የምርምር ውጤቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ
መንታ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ የአጥንት መገጣጠሚያዎች
ችግር የመጠቃት እድል እንደሚጨምር ነው ፡፡ ስለሆነም የዚህ ዓይነቱ
የቀዳማዊ የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር 60 በመቶ ያህል የሚሆነው
የሚመጣው በቤተሰብ የዘር ሐረግ መሃል ሊኖር በሚችል ተመሳሳይ
ችግር ምክንያት ነው ፡፡
2. ሁለተኛ ደረጃ የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር
ይህ የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር ከቀዳማዊ የአጥንት
መገጣጠሚያዎች ችግር ጋር ተመሳሳይ የሆነ የህመም ዓይነት ቢሆንም
መነሻ ምክንያቱ ግን ይለያያል ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው ፡፡
– የመገጣጠሚያ አካላት በተፈጥሮ ችግር ኖሮባቸው መፈጠር
– የስኳር ህመም
– የሪህ ህመም
– በነዚህ አካባቢዎች የተፈጠረ አደጋ
– የሠውነት ክብደት መጨመር
የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር መከሰት ምልክቶች
– ጡንቻዎችን የመለብለብ ስሜት መኖር
– በመገጣጠሚያዎች አካባቢ በተለይ በታፈነና በቀዝቃዛ የአየር ሁኔታዎች
ወቅት የሚኖር የህመም ስሜት
– የጡንቻዎች መኮማተር
– በችግሩ የተጠቁ አካባቢዎች እብጠት ማሳየት እና የህመም ስሜት
– በቁርጭምጭሚት መጋጠሚያዎች አካባቢ የፈሳሽ መጠራቀም
የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግርን ለመቆጣጠር የሚረዱ መንገዶች
– የሠውነት ክብደትን መቆጣጠር
– በባለሙያ በመታገዝ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ
– መድኃኒቶችን በሐኪም ትእዛዝ መሠረት ብቻ መጠቀም