የዓይን ብዥታ( Astigmatism or Distorted Vision)

የዓይን ብዥታ የኦፕቲካል ችግር ሆኖ የሚታዩ ነገሮች ብዥ ብለው መታየት
ሲጀምሩና ዓይናችን ላይ አርፎ መልስ የሚሰጥበት ሂደት ሲዛባ የሚፈጠር
ክስተት ይሆናል ፡፡ ይህ ደግሞ ኮርኒያ ወይንም ሌንስ ላይ የሚያርፈው
የምስል ቅርፅ በአግባቡ ሳይሆን የሚፈጠር ነው ፡፡
የዓይን ብዥታ ግራ የሚያጋባ የማየት ችግር ነው ፡፡ እንደ የቅርብና የሩቅ
የማየት ችግር ሁሉ የዓይን ብዥታ ችግርም ምስሎች ዓይን ውስጥ
በአግባቡ ካለማረፋቸው የተነሳ የሚከሰት ነው ፡፡ ይህ ማለት ችግሩ
የዓይን ጤና ማጣት ችግር አይደለም ማለት ነው ፡፡ ከዚህ ይልቅ በቀላሉ
ወደ ዓይን የሚገባው ብርሃን በአግባቡ አለመስተናገዱ ይሆናል ማለት ነው
፡፡ ችግሩ ያለበት ግለሠብ ዓይን ውስጥ ብርሃን ሲገባ ሬቲና ላይ ማረፍ
ሲገባው ከፊት ወይንም ከኋላ ወይንም ሁለቱም ላይ ያርፋል ፡፡
የዓይን ብ»ታ መነሻ ምክንያቶች
የዓይን ብዥታ ችግር ብዙ ጊዜ የሚከሰተው ኮርኒያ ተብሎ የሚጠራው
የዓይን ክፍል ትክክለኛውን ቅርፅ ሳይዝ ሲቀር ነው ፡፡ ይህ የዓይን ክፍል
የቤዝቦል መጫወቻ ኳስ ቅርፅ መያዝ ሲገባው የእግር ኳስ የሚመስል ክብ
ቅርፅን ይይዛል ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በዓይን ውስጥ ያለው ሌንስ ከጤነኛው ቅርፅ ተለይቶ
ሲገኝ የዓይን ብዥታ ችግር ሊከሰት ይችላል ፡፡
የዓይን ብዥታ ችግር ምርመራ
ይህ የዓይን ችግር ዓይነት እንደ የቅርብና የሩቅ የማየት ችግር ሁሉ
ምርመራውም በተመሳሳይ መሳሪያዎችና የምርመራ ዓይነቶች ሊሆን
ይችላል ፡፡